loading
የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ከ200 ሺህ በላይ ቁጥር ላላቸዉ ሴቶች የነጻ የህግ አገልግሎት ሰጥቼያለሁ አለ፡፡

የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ከ200 ሺህ በላይ ቁጥር ላላቸዉ ሴቶች የነጻ የህግ አገልግሎት ሰጥቼያለሁ አለ፡፡

ማህበሩ ለአርትስ በላከዉ መረጃ  የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ከተመሰረተበት ከ1987ዓ.ም ጀምሮ አስካሁን ከ200 ሺህ በላይ ቁጥር ላላቸዉ ሴቶች እና የዚህ እጥፍ ቁጥር ላላቸዉ ህጻናት ነጻ የህግ አገልግሎት መስጠቱን ገልጿል፡፡

በማህበረሰባችን ዉስጥ የጾታ እኩልነትን በተመለከተ የተዘባ አመለካከት ለማጥፋት  የሴቶች መብት እና የጾታዊ ጥቃትን መከላከል በተመለከተ ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራቱንም ገልጿል፡፡

በፍትህ አስተዳደሩ ዉስጥም የጾታ እኩልነት ተቆርቋሪ ስርዓት እንዲሰፍን አስተዋጽኦ ለማድግ ለሕግ አውጪዉ፤አስፈጻሚና ተርጓሚ ባለድርሻ አካላት በጾታ እኩልነት ላይ ስልጠና ሰጥቷል፡፡በዚህም 80 ሺህ በላይ ሰዎችን በቀጥታ፤ በተዘዋዋሪ ደግሞ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን በመድረስ የሴቶች ጉዳይ ብሔራዊ አጀንዳ እንዲሆን ሰርቼያለሁ ብሏል፡፡

ማሀበሩ በአዲስ አበባ ካለዉ ዋና ጽ/ቤት በተጨማሪ በአዳማ፤በሃዋሳ በባህርዳር በጋምቤላ በአሶሳ በድሬደዋ እና በዘጠኙም ክ/ከተሞችና በገጠር ከተሞች አካባቢ በሚገኘዉ በ54 በጎ ፍቃደኛ ኮሚቴዎች አማካኝነት ነጻ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ማህበሩም አለም አቀፍ የሴቶችን ቀን አስመልክቶ ‘’ኑ  የሴቶችን ጥበብ እና ስኬት እናጣጥም ’’በሚል የካቲት 28 ከቀኑ 11ሰዓት ላይ በማኪ አርት ጋለሪ ልዩ የጥበብ ፕሮግራም አዘጋጅቼያሉ ብሏችኋል፡፡

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *