የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ላኪዎች በ24ኛው የገልፍ ፉድ ኤግዚቢሽን ላይ እየተሳተፉ ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ላኪዎች በ24ኛው የገልፍ ፉድ ኤግዚቢሽን ላይ እየተሳተፉ ነዉ፡፡
በምግብ ምርቶች ላይ በማተኮር ከየካቲት 10 እስከ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በዱባይ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን ማዕከል በሚካሄደው በ24ኛው የገልፍ ፉድ 2019 ኤግዚቢሽን ከ187 በላይ የአገራችን የወጪ ምርቶች ላኪዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
በኤግዚቢሽኑም 63 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሽያጭ ለማከናወን እቅድ ተይዟል።
በፕሮግራሙ የቡና፣የስጋ፣የቅባት እህሎች ጥራጥሬ ፣ቅመማ ቅመም ፣የእንስሳትና የማር ምርቶች ቀርበዋል። በተጨማሪም የአገራችንን የቱሪዝም ሀብቶች ባህላዊ ምግቦችና የቡና አፈላል ስነስርዓት የሚያስተዋውቅ ፕሮግራም ቀርቧል።
ለአገራችን የወጪ ምርቶች ሰፊ የገበያ ዕድል እንደሚገኝበት በሚታመነውን በዚሁ ኤግዚቢሽን ላይ የአገራችን የወጪ ምርቶች ማሳያ (ፓቪሊዮን) በኢፌዲሪ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋና በዱባይና በሰሜን ኤሜሬቶች በዱባይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ወ/ሮ እየሩሳሌም አምደማሪያም ተከፍቷል።