loading
የኢትዮ-ኬንያ የጋራ የድንበር ያለበትን ሁኔታ የሚገመግመዉ ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡

የኢትዮ-ኬንያ የጋራ የድንበር ያለበትን ሁኔታ የሚገመግመዉ ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡

የኢትዮ-ኬንያ የጋራ የድንበር ኮሚሽን ስብሳባ የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች የችካል አጠባበቅ እና ግምገማ የሚያካሄዱበትን ቀነ-ገደብ ለማስቀመጥ ተስማምተዋል።

ከግንቦት 5 እስከ 9 ቀን በሞምባሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 32ኛው የኮሚሽኑ ጉባኤ በተጨማሪም ለስራው የሚያገለግል በጀትን የማሰናዳት ጉዳዮች ላይ ውይይት በማካሄድ በጀት አጽድቀዋል።

በኬንያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም በስብሰባው ዝግጅት ላይ በመገኘት የመዝጊያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፥ በወቅቱም በኢትዮጵያ እና ኬንያ መካከል ያለው ግኑኝነት ታሪካዊ መሰረት ያለው እና ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለረዥም ጊዜና ሳይቆራረጥ የመጣ መልካም የሁለትዮሽ ወዳጅነት እንዳላቸው በመግለፅ ይህ ግንኙነት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ወደ ላቀ የህዝብ-ለህዝብ ግንኙነት መሸጋገር እንዳለበት ገልጸዋል።

ሁለቱም ወገኖች ስምምነቶቹን ለመተግበር የሚያስችል ቃለ-ጉባኤ በልዑካን ቡድን መሪዎቻቸው አማካኝነት ተፈራርመዋል።
የዉጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃላአቀባይ ጽ/ቤት እንዳስታወቀዉ የኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር እ.ኤ.አ 1950 እስከ 1955 መካለሉ የሚታወስ ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *