loading
የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የዕርቀ ሰላም ልዑኳን ወደ አሜሪካ ሸኘች፡፡

የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የዕርቀ ሰላም ልዑኳን ወደ አሜሪካ ሸኘች፡፡

በውጭ አገር ከሚኖሩ ብፁዓን አባቶች ጋር እየተደረገ ባለው የዕርቀ ሰላም ሂደት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ለዕርቀ ሰላም ልዑካን አባላት የሽኝት መርሐ-ግብር ተደርጎላቸዋል፡፡

አቡነ ማትያስ በሽኝት ስነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ቤተ ክርስቲያን ለዚህ ዕርቀ ሰላም ሂደት የበኩሏን ጥረት ስታደርግ መቆየቷን አስታውሰው፤ የዕርቀ ሰላሙ ሂደት ወደ ፍጻሜ ማምራት እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡

የዕርቀ ሰላም ኮሚቴ አባላትም ላቀረቡት የዕርቀ ሰላም ጥያቄ ከቅዱስ ፓትርያርኩና ከቅዱስ ሲኖዶስ ላገኙት አዎንታዊ መልስና ቀና ትብብር ምስጋናቸውን ገልጸው፤ የተጀመረው ዕርቀ ሰላም በመልካም ፍጻሜ እንዲቋጭ አሁንም ድጋፋቸውና ጸሎታቸው እንዳይለያቸው ተማጽነዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *