የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለቴክኖሎጂ ቅርብ የሆነው ወጣት የዲጂታል እውቀት እንዲኖረው ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ::
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 12፣ 2013 የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለቴክኖሎጂ ቅርብ የሆነው ወጣት የዲጂታል እውቀት እንዲኖረው ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ::ሚኒስቴሩ የጤና ጉዞ ወደ ኪቢቃሎ ተራራ በሚል በወልዲያ ከተማ ተራራ ላይ በተደረገው ጉዞ ላይ ለተሳተፉ ወጣቶች የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን አስተዋውቋል።የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሀመድ ለቴክኖሎጂ ቅርብ የሆነውን ወጣት የዲጂታል እውቀት እንዲኖረው ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል።
አብዛኞቹ ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ በመሆናቸው ዲጂታል እውቀት በመጨመር ቴክኖሎጂን ለጤና፣ ቴክኖሎጂን ለንግድና ቴክኖሎጂን ለመልካም ነገር እንዲያውሉት ጠይቀዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ ከደሴ ኮምቦልቻ ጉዞ በማድረግ የተጀመረው የእግር ጉዞ 7ኛው ዙር ወደ ኪቢቃሎ ተራራ የተደረገ ሲሆን ከኮምቦልቻ እስከ ደሴ ያሉ ወጣቶች ተሳትፈውበታል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን በተለያዩ አካባቢዎች የማስተዋወቁ አንድ አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡