loading
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያን ጎበኙ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያን ጎበኙ

ፕሬዚዳንቷ በጉብኝታቸው ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ከ60 ሽህ በላይ የሚሆኑ ወጣት ኢትዮጵያዊያንን በማከም ከፊስቱላ ህመም መፈወስ የቻለ አንጋፋ ድርጅት ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ድርጅቱ ንፁህና ሳቢ ተቋም መስርቶ ከሚሰጠው ዘመናዊ ህክምና ባለፈ አዋላጅ ነርሶችን በብቃት እያሰለጠነ ለሌሎች የህክምና ተቋማት ጭምር ከፍተኛ ደጋፍ በማድረግ ላይ የሚገኝ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለውለታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የድርጅቱ መስራች የዶ/ር ካትሪን ሐምሊን 95ኛ ዓመት የልደት በዓላቸው ተከብሯል፡፡ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴም የዶክተር ካትሪን ቀጣይ ጊዜ መልካም እንዲሆን ምኞታቸውን አስተላልፈዋል ፣ ከፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *