loading
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጅቡቲን ሊጎበኙ መሆኑ ተገለፀ

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጅቡቲን ሊጎበኙ መሆኑ ተገለፀ

አርትስ 27/03/2011

 የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  በትናትናው ዕለት  ይፋ እንዳደረጉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በቅርቡ ሀገሪቱን ይጎበኛሉ ብለዋል።

አናዶሉ የዜና ወኪልን ጠቅሶ ፋና እንደዘገበው ሁለቱ ሀገራት በኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ በመካከላቸው የነበረውን ልዩነት ለመፍታት በከፍተኛ መሪዎች ደረጃ ግንኙነት ሲያደርጉ እንደቆዩ ነው የተጠቆመው።

መሪዎቹ የሚገናኙበት ቀን እንዳልተቆረጠ የተገለፀ ሲሆን፥ ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች  በየሀገራቶቻቸው ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሃመድ አሊ ዮሱፍ አስታውቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኤርትራ አቻቸው ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን ገልጸው ፥  በሀገራቱ መካከል መተማመንን ለማሳደግ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ ቀንድ  ሰላምና ብልፅግናን ለማምጣት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የእርቅ ሂደቱን ማስጀመራቸውን በመግለፅ አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *