loading
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ስራቸውን ለቀቁ

አርትስ 06/03/2011

 

መከላከያ ሚኒስትሩ አቭግዶር ሌበርማን ስራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንዲለቁ ያሰገደዳቸው በእራኤልና በጋዛ መካከል የተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት መሆኑን በጋዜጣዊ መግለጫቸው ተናግረዋል፡፡

ከሀማስ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት መፈራረም ለሽብርተኝነት እጅ መስጠት ነው ያሉት  ሌበርማን ሀገሬ ለጊዜያዊ መፍትሄ ስትል ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍላትን ስህተት ሰርታለች ብለዋል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታናያሁ ጋር  ቁርሾ ውስጥ መሆናቸው ሚስጥር እንዳልሆነ ይፋ አድርገዋል፡፡

በጋዜጣዊ በግለጫው ወቅት እኔና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበርካታ ነገሮች አልተስማማንም፡፡ ይሁን እንጂ የተጋጨንባቸውን ሃሳቦች ሁሉ መዘርዘር አይጠበቅብኝም ነው ያሉት፡፡

ሌበርማን አክለውም እስካሁን መንግስት በሰጠኝ ሀላፊነት ሀገሬን ምንጊዜም በታማኝነት  ለማገልገል ሞክሬያለሁ በማለትም ተናግረዋል፡፡

ኔታናያሁ በበኩላቸው በመሪነት ቦታ ያሉ ሰዎች ሁሌም ከትችት አያመልጡም፤ ውሳኔያችን ከባድ ቢመስልም ሀማስ ስለለመነን አድርገነዋል በማለት  ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *