loading
የእስራኤል ተዋጊ ጄቶች በጋዛ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ተነገረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 የእስራኤል ተዋጊ ጄቶች በጋዛ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ተነገረ፡፡ እስራኤል በዚህ ሳምንት ለሁለተኛ ጊዜ በማእከላዊ ጋዛ ሰርጥ የአየር ጥቃት መፈፀሟ ተነግሯል፡፡ አልጄዚራ የዐይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው የእስራኤል ተዋጊ ጄቶች የሮኬት ሞተሮችን ከሚያመርተው እና ከመሬት በታች በሚገኘው ህንፃ ላይ ጥቃት አድርሰዋል።


የመረጃ ምንጩ ይሄንን ዘገባ እስካጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በጥቃቶቹ በማዕከላዊ ጋዛ በሚገኘው አል ቡሬጅ የስደተኞች ካምፕ የሚገኙ በርካታ ቤቶች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በሰው ህይወት ላይ ስለደረሰ ጉዳት የተገለጸ ነገር የለም። ከዚህ ጥቃት በፊት ከጋዛ በኩል የተተኮሰ ሮኬት በደቡባዊ እስራኤል መኖሪያ ቤት ላይ መጠነኛ ጉዳት
ቢያደርስም የከፋ ጉዳት አላስከተለም ሲል የእስራኤል ፖሊስ ተናግሯል።


ከጋዛ አራት ተጨማሪ ሮኬቶች እንደተተኮሱ የእስራኤል ጦር ሃይል ያስታወቀ ሲሆን ነገር ግን በአየር መከላከያ ዘዴዎች እንዲመክኑ ሆነዋል ብሏል። ይሁን እንጂ ለሮኬቱ ጥቃት ሃላፊነቱን የወሰደ የትኛውም የፍልስጤም ቡድን የለም ተብሏል። ጋዛን የሚያስተዳድረው ሃማስ ባወጣው መግለጫ የእስራኤል የቦምብ ጥቃት ፍልስጤማዊያን
ወረራውን ተቋቁመው እንዲመክቱ እና ለእየሩሳሌም እና ህዝቦቿ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ እንደሚያግዛቸው አስታውቋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *