loading
የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር የርገን ክሎፕ ላይ የ8 ሺ ፓውንድ ቅጣት ይጥላል ተባለ

የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር የርገን ክሎፕ ላይ የ8 ሺ ፓውንድ ቅጣት ይጥላል ተባለ

አርትስ ስፖርት 26/03/2011

በ14ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መርሀ ግብር በመርሲ ሳድ ደርቢ በአንፊልድ ሮድ ስታድየም ሊቨርፑል ከ ኢቨርተን ባደረጉት ጨዋታ ባለቀ ሰዓት በ96ኛው ደቂቃ ዲቮክ ኦሪጊ ባስቆጠራት ግብ ቀያዮቹ 1 ለ 0  ሲረቱ፤ ግቧ በተቆጠረበት ቅፅበት አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ወደ ሜዳ በመግባት ከግብ ጠባቂው አሊሰን ቤከር ጋር ባሳዩት ፌሽታ፤ ለተቃራኒ ቡድን ክብር ባለመስጠት ከፍተኛ ውግዘት ደርሶባቸዋል፡፡

እርሳቸውም በድርጊታቸው መፀፀታቸውን ተናግረዋል፡፡

የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበርም በዚህ ድርጊታቸው ክስ አቅርቦ እስከ ሀሙስ ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቆ ነበር፤ ክሎፕም ክሱን እንደሚቀበሉ አስታውቀዋል፡፡

ማህበሩ የ8 ሺ ፓውንድ ቅጣት ይጥልባቸዋል የተባለ ሲሆን ከእንዲህ አይነት ባህሪያቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *