loading
የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ኦዲፒ ኦነግ በተለያዩ ዞኖች ወታደራዊ ስልጠና እያካሄደ ነው ሲል ከሰሰ

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ኦዲፒ ኦነግ በተለያዩ ዞኖች ወታደራዊ ስልጠና እያካሄደ ነው ሲል ከሰሰ

አርትሰ ታህሳስ 19 2011

 የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊው አቶ አዲሱ አረጋ በሰጡት መግለጫ ኦነግ በተለያዩ ዞኖች እንደ አዲስ ጦር መልምሎ እያሰለጠነ ነው

አቶ አዲሱ በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን እና ከኤርትራ የገቡትን የኦነግ ሰራዊቶችን በማሰልጠን እንደየ አስፈላጊነቱ የጸጥታ ኃይሉን እንዲቀላቀሉ ወይም በሌሎች መስኮች እንዲሰማሩ ለማድረግ ከኦነግ ጋር ከስምምነት መድረሳቸውን አስታውሰዋል፡፡

በሃገር ውስጥ የሚገኙ የኦነግ ወታደሮችን ከኤርትራ ከተመለሱት ጋር በአንድ ላይ ሰልጠና ለማስጀመር ብንሞክርም በሃገር ውስጥ ያሉት ግን አልተገኙም ነው ያሉት።

በመንግሥት እና በኦነግ መካከል የተደረሰውን ስምምነት ለማስፈጻም ከሁለቱም ወገን ተወካዮች በተዋቀረው ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በሚደረጉ ውይይቶች ከስምምነት ይደረሳል፤ ተፈጻሚ ግን አይሆኑም ብለዋል።

የኦነግ አመራር በጠቅላለው ሰላማዊ ትግልን እንደ አማራጭ አድርጎ መቀበሉ አጠራጥሮናል የሚሉት አቶ አዲሱ፤ የኦነግ አመራር እና በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኙ የጦር አመራሮች የሚሰጡት መግለጫዎች የተለያዩ ናቸው ይላሉ።

ኦነግ በጉጂ፣ ቄለም፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ እና ኢሉ አባቦራ ዞኖች ውስጥ አዲስ ጦር መልምሎ እያሰለጠነ ነው ይህም እጅጉን ያሳስበናል ብለዋል አቶ አዲሱ።

 

አቶ አዲሱ ጨምረውም ሕገ-ወጥነት እየተስፋፋ ነው፤ አመራሮቻችንም እየተገደሉ ነው ብለዋል። በሌላ በኩል ከቀናት በፊት የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ፓርቲያቸው ከመንግሥት ጋር ከስምምነት ላይ የደረሰባቸው ጉዳዮች በመንግሥት እየተጣሱ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *