loading
የካራባዎ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በቼልሲ እና ማንችስተር ሲቲ መካከል ዛሬ ይካሄዳል ::

የካራባዎ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በቼልሲ እና ማንችስተር ሲቲ መካከል ዛሬ ይካሄዳል ::

 

 

የእንግሊዝ እግር ኳስ ሊግ ዋንጫ አሊያም በስፖንሰር አድራጊው ካራባዎ ስም የሚጠራው ይህ ውድድር፤ የፍፃሜ ግጥሚያ በቼልሲ እና ማንችስተር ሲቲ መካከል ዌምብሌይ ስታዲየም ላይ ምሽት 1፡30 ይከናወናል፡፡

 

 

በምሽቱ የዋንጫ ጨዋታ ሰማያዊዎቹ በሊጉ በሲቲ ግማሽ ደርዘን ጎል ተቆጥሮባቸው ሲሸነፉ፤ ከኤፍ ኤ ዋንጫ በማንችስተር ዩናይትድ መሰናበት የአሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪን ስራ አጣብቂኝ ውስጥ ከትቶታል፡፡

 

 

 

ክለቡ የዋና ግብ ጠባቂውን ኬፓ አሪዛባላጋን ግልጋሎት የማያገኝ ሲሆን፤ ለአራት ዋንጫ እየተንደረደረ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ በኩል ጓርዲዮላ ግቡ እንዲጠበቅለት ዋናውን ኤደርሰን ሞራኤስን ወይስ አሪያኔት ሙሪችን መመረጥ ይጠበቅበታል፡፡

 

 

ለቼልሲዎች የተከላካዩ ዳቪድ ዛፓኮስታ እና አጥቂው ፔድሮ ካለባቸው ህመም አገግመው የመሰለፋቸው ነገር አጠራጣሪ ነው ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *