loading
የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች ባሉበት ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ ለውጡን አደጋ ላይ ይጥለዋል አሉ የዓርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

አርትስ 22/04/2011
የፌዴራል መንግሥት የማይቆጣጠራቸው ከ10 ሺህ እስከ 20 ሺህ የሚቆጠሩ የፀጥታ ኃይሎች በየክልሉ መኖር ቀጣዩን አገራዊ ምርጫ አዳጋች ሊያደርጉ ከሚችሉ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ በመሆኑ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰሩ  ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ እነዚህ ታዛዥነታቸው ለክልሉ የሆኑ ኃይሎች አንድ ድርጅት ወደዛ ሄዶ እንቅስቃሴ ማድረግ ቢፈልግ እንኳ ጦር የያዙ ሰዎች ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ አይታወቅም፡፡ ይህም ከበፊቱ ሥርዓት የተወረሱ ያልተላቀቁ ሃሳቦች አሁንምእንዳሉ አመላካች ይሆናል ብለዋል፡፡
እንደፕሮፌሰር ብርሃኑ ገለፃ በየክልሉ ይህን መሠል ትልቅ ኃይል ይዘው ማን ይነካናል? የሚሉ እንዲሁም ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን የሚደብቁ በመኖራቸው ችግሮቹን ለመፍታት ሰፊ ሥራ ይጠይቃል፡፡

በመሆኑም እነዚህና መሠል ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ መፍትሔ ሳይበጅላቸውና ሳይረጋገጡ ምርጫ ማድረግ አገሪቱን ወደ ከፋ ቀውስ ይከታል፡፡ ችግሮች ሳይፈቱም የምርጫውን ቀን መወሰን አይገባም፡፡

ለምርጫውና በቀጣይ በአገሪቱ ለመገንባት የታቀደውን ዕውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ቅድሚያ ሊሠሩ ከሚገባቸው ጉዳዮች መካከልም አንዱ በየክልሉ የሚገኘው የፀጥታ ኃይል ሊሠራበት እንደሚገባም ነው ሊቀመንበሩ የተናገሩት፡፡

አልያ ግን ምርጫ መደረግ አለበት በሚል ብቻ ቅድሚያ መከናወን የሚገባቸው ተግባራት ሳይጠናቀቁ ወደዛ ማምራት እጅጉን አስቸጋሪና ለውጡንም መቀልበስ ይሆናል፤ በመሆኑም በሕግ እርምጃ መውሰድ ያለበትና በየደረጃው ተጠያቂ ማድረግ የሚገባውም የፌዴራልመንግሥት ብቻ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *