የኮሮና ቫይረስ በ164 ሰዎች ላይ ሲገኝባቸው፤ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 የኮሮና ቫይረስ በ164 ሰዎች ላይ ሲገኝባቸው፤ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 630 የላብራቶሪ ምርመራ 190 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 670 መድረሱንም የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ባወጡት ሪፖርት አመላክተዋል። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 163ቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ አንዱ የዉጭ ሃገር ዜጋ ነዉ፡፡ እድሜያቸው ከ1 እስከ 92 ዓመት የሆኑ 117 ወንዶችና 47 ሴቶች ናቸው።ቫይረሱ በምርመራ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 104 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፥26 ሰዎች ከሶማሌ ክልል 22 ሰዎች ከአማራ ፣ 4 ሰዎች ከትግራይ 4 ሰዎች ከደቡብ 2 ሰዎች ከኦሮሚያ ፣1 ሰዉ ከሐረሪ ፣ ፣ እንዲሁም 1 ሰዉ ከቤኒሻንጉል ክልል ናቸው።ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የአምስት ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉንም ዶክተር ሊያ በሪፖርታቸው አመላክተዋል።
ህይወታቸው ያለፈው አራቱ ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፤ አንድ ከሱማሌ ክልል ነዉ፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 40 መድረሱን ተጠቁሟል፡፡ በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 33 ሰዎች (32 ከአዲስ አበባ፣ 1 ከአማራ ክልል) ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 434 መድረሱንም ታውቋል።