loading
የኮንጎ አማፂዎች የሰላም አስከባሪዎችን ገደሉ

አርትስ /07/03/2011
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዲሞካራቲክ ኮንጎ የሚገኙ 7 የሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ
እንደተገደሉበት ይፋ አድርጓል፡፡
ዘ ዋ ሽግተን ፖስት እንደዘገበው የሰላም አስከባሪዎቹ ራሱን የተባበሩት ዴሞክራሲያዊ ሀይሎች ብሎ
ከሚየጠራው የታጣቂ ቡድን ጋር ባካሄዱት ውጊያ ነው የተገደሉት፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክ ከተገደሉት በተጨማሪ አስር ወታደሮች
መቁሰላቸውንና አንድ ደግሞ የገባበት አለመታወቁን ገልጸዋል፡፡
የድርጅቱ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የኮንጎ አማፂያን በሀገሪቱ የሚፈፅሙትን አለመረጋጋት
እንዲያቆሙና ትጥቃቸውን በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪ ማቅረባቸውን ዱጃሪክ ተናግረዋል፡፡
ከሞቱት ወታደሮች መካከል ስድስቱ የማላዊ ዜግነት ያላች ሲሆን አንዱ ደግሞ ከታንዛኒያ መሆኑ
ታውቋል፡፡
ተቃዋሚ ሀይሎቹ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጠጠር ከ2014 ጀምሮ 1 ሺህ 500 ንጹሀን ዜጎችን
መግደላቸውን ሪፖርቱ ያሳያሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *