loading
የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች የመንግሥትን አፋጣኝ እርምጃ ጠየቁ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 የህዋሓት ቡድን ነሀሴ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽቱን ወደ ወልድያ ከተማ በተደጋጋሚ ከባድ መሣሪያ መወርወሩን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡

ነዋሪዎቹ መንግሥት በህዋሓት ቡድን ላይ የአካባቢውን ሕዝብ የትግል ጥንካሬ በመጠቀም ፈጣን እርምጃ መውሰድ ባለመቻሉ የሽብር ቡድኑ ከተማዋን ለማውደም ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ከባድ መሣሪያ መወርወር ጀምሯል ብለዋል።

መንግሥት ለሠላም ዋጋ የሚከፍልን ሕዝብ በከባድ መሣሪያ ለማውደም ሙከራ ሲደረግባት አቅም እያለው እስከዚህ ድረስ ማድረሱ ስህተት ነው፤ አሁንም ቢረፍድም ለእርምጃ አልመሸም ሲሉ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

ከወደብ የሚመጣው የህዳሴ ግድቡ የግንባታ ማሽን የሚያልፍባት፤ ልዩ ልዩ ፋብሪካዎች እና በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ “መሐመድ ሁሴን ዓሊ አል-አሙዲ ስታድየም ” የሚገኝባትን ከተማ እና ለሰላም ዋጋ እየከፈለ ያለን ህብረተሰብ የበቀል መወጫ ማስደረግ ከመንግሥት አይጠበቅም ብለዋል አስተያየት ሰጭዎቹ።

መንግሥት በጠላት እቅድ እንጂ በእራሱ እቅድ ነድፎ ያለውን የወልድያ ወጣቶች ያልተቋረጠ ደጀንነት በመጠቀም አጥቅቶ ጠላትን ከመጠራረግ ይልቅ ለጠላት ረጅም ጊዜ በአካባቢው እንድቆይና እንዲጠናከር ማደረጉ ለከተማ ነዋሪው ስጋት ከመፍጠሩም ባለፈ ውስጣችን ጥርጣሬን እየጫረብን ነዉ ማለታቸዉን ከወልድያ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ፌስቡክ ገፅ ነያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *