loading
የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች ለህብረተሰቡ መድረሳቸውን የሚያረጋግጥ ጠንካራ የቁጥጥር ስርአት መዘርጋት እንደሚገባ ምክር ቤቱ አሳሰበ።

የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች ለህብረተሰቡ መድረሳቸውን የሚያረጋግጥ ጠንካራ የቁጥጥር ስርአት መዘርጋት እንደሚገባ ምክር ቤቱ አሳሰበ። 
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 5ኛ መደበኛ ስብሰባ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርን የ8 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ሲገመግም በኑሮ ውድናትና ህገ-ወጥነት ላይ ትኩረት አድርጎ ተወያይቷል።


ሚኒስትሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላ በወጪ ንግድ ገቢ፣ የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች አቅርቦትና ስርጭት፣ እንዲሁም የአሰራር ስርዓቶች ዙሪያ ባለፉት 8 ወራት የተከናወኑ
ተግባራት ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።  የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት መንግስት የውጭ ምንዛሬ በመመደብ ለፋብሪካዎች  ድፍድፍ ዘይት እንዲቀርብ በማድረግ ከ103 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት በአገር ውስጥ ተመርቶ እንዲሰራጭ መደረጉን ገልጸዋል።


ይህም በ8 ወራት ውስጥ መቅረብ ካለበት 320 ሚሊዮን ሊትር ፍላጎት ጋር ሲነጻጸር 32 ነጥብ 4 በመቶ ድርሻ እንዳለው አመላክተዋል። እንደ ሚኒስትር ገለጻ፤ የስንዴ ፍላጎት ጉድለትን ለመሙላት ግዥ ከተፈጸመው 4 ሚሊዮን ኩንታል ውስጥ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታሉን ለማሰራጨት ታቅዶ 670 ሺህ ተሰራጭቷል።
የምክር ቤቱ አባላት የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ መንግስት የኑሮ ውድነትና የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት እርምጃ እየወሰደ ቢሆንም ችግሩ አሁንም መቀጠሉን አንስተዋል። የሸቀጦችና የግንባታ እቃዎች መናር፣ ህገ-ወጥነት፣ ሌብነትና ሌሎች በንግድ ስርዓቱ ውስጥ የሚስተዋሉ ችግሮች ህብረተሰቡን እያማረሩ መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *