የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲሱን የመዋቅር ማሻሻያ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ
አርትስ 29/02/2011
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያካሄደው የአደረጃጀት ማሻሻያ በመዋቅር፣ በሰው ሃይል ምደባና ስምሪት እንዲሁም በመሰረተ ልማትና አቅም ግንባታ ላይ ያተኮረ እንደነበር የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ቃል አቀባዩ አቶ መለስ ዓለም በሳምንታዊ መግለጫቸው ላይ እንዳስታወቁት ሚኒስቴሩ አዲስ በተቀረጸው መዋቅር እና አደረጃጀት ስራ ጀምሯል።
ለዚህ አዲስ አደረጃጀትም አምስት ቋሚ ተጠሪዎችና 31 የከፍተኛ አመራር አባላትን ሹመት ማካሄዱን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የሚሲዮኖችና የአምባሳደሮች ምደባ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
መዋቅራዊ ለውጡ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም የበለጠ የሚያስከብርና አህጉራዊና ዓለማ ቀፋዊ ሀላፊነቶችን በአግባቡ እንድትወጣ የሚያስችላት መሆኑንም ተናግረዋል፡