loading
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ.ኤም.ኤፍ) ልዑክ የሀገሪቱን የአውሮፓውያኑ የ2018 ዓመታዊ ኢኮኖሚ ግምገማ ለማድረግ አዲስ አበባ ገብቷል።

አርትስ 02/01/2011

በሚስተር ጁሊዮ ኤስኮላኖ የሚመራው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ.ኤም.ኤፍ) ልዑክ በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆይታ በኢኮኖሚ ዕድገት፣ በፊሲካል ፖሊሲ፣ በገንዘብና ፋይናንስ ዘርፍ እና በውጭ ዘርፍ ዙሪያ አፈጻጸሞችን እንደሚገመግም ይጠበቃል።
ቡድኑ በዋናነት በ2010 የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸሞችና በቀጣዮቹ ዓመታት ዕይታ ላይ ግምገማ እንደሚያደርግ የሚጠበቅ ሲሆን፥ በመጨረሻው የግምገማ ምዕራፍም የግምገማ ረቂቅ ሪፖርት በማዘጋጀት ለሀገሪቱ ፖሊሲ አውጭዎች እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።
በተጨማሪም ልዑካን ቡድኑ በቆይታው ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ተገናኝቶ በጉዳዩ ላይ ሀሳብ በመለዋወጥ እንደሚመክርም ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የዓለም ገንዘብ ድርጅት ልዑኩ በዛሬው እለት ስራውን የጀመረ ሲሆን፥ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶክተር አብረሃም ተከስተ እና ከብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ጋር ተገናኝቶ ውይይት አድርጓል።
ኤፍ.ቢ.ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *