loading
የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛው የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር መመዝገቡ እንዳሳሰበው ገለፀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛው የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር መመዝገቡ እንዳሳሰበው ገለፀ:: ድርጅቱ በሰጠው መግለጫ በ24 ሰዓታት ውስጥ በዓለም ከ307 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መያዛቸው ሪፖርት ደርሶኛል ብሏል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ከሁሉም ሀገራት የበለጠ ከፍተኛውን ቁጥር ያስመዘገቡት ህንድ አሜሪካና ብራዚል ናቸው፡፡ እንደሪፖርቱ በሳምንቱ መጨረሻ ህንድ 94 ሺህ 372፣ አሜሪካ 45 ሺህ 523፣ ብራዚል ደግሞ 43 ሺህ 718 ዜጎቻቸው በ24 ሰዓታት በቫይረሱ ተይዘውባቸዋል፡፡

በዓለም በቫይረሱ የተያዙተረ ሰዎች ከ19 ሚሊዮን በላይ ያሻቀበ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ ከ917 በላይ ደርሷል፡፡ በቫይረሱ ስርጭት ከዓለም ቀዳሚ የሆነችው አሜሪካ የዓለምን አነውድ አራተኛ የሚሆነውን ቁጥር ስትይዝ ህንድና ብራዚልም በቅርብ እርቀት እየተተሏት ነው፡፡ ቫይረሱ በበርካታ ሀገራት ዳግም እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ ብዙ ሀገሮች የእንቅስቃሴ እቀባዎች እንደ አዲስ መጣል መጀመራቸውም ተሰምቷል፡፡ ለዚህም በአውሮፓ ሀገራት የእየታየ ያለው የአካላዊ እርቀት እና የፊት መሸፈኛ ጭንብል አሰገዳጅ ህጎች መደንገግ እንዲሁም አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን የመዝጋት እንቅስቃሴ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *