loading
የዓለም ጤና ድርጅት የማህበረሰብ ጤና ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳሰበ ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2012 የዓለም ጤና ድርጅት የማህበረሰብ ጤና ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳሰበ ::ድርጅቱ ለዓለም መሪዎች ባስተላለፈው ጥሪ የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመግታትና የዜጎችን ህይዎት ለመታደግ ሁነኛው መፍትሄ የማህበሰረብ ጤናን ማጠናከር ነው ብሏል፡፡ ሀገራት የጤና ፖሊሲዎቻቸውን መፍትሄ አምጭ ማድረግና ተግባራዊነታቸውን ማረጋገጥ ተገቢ ነው ያለው የዓለም ጤና ድርጅት በተለይ በዚህ ወቅት ሁሉም የሀገራት መሪዎች ብልህነት የታከለበትአመራር መስጠት ላይ ማተኮር አለባቸው ሲል አሳስቧል፡፡ የድርጅቱ ዋና ዳይክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች ተከታትሎ መለየት፣የተለዩትን ሰዎች ከንክኪ ማራቅ፣ እንክብካቤ ማድረግና ምርመራን በስፋት ማከናወን ያስፈልጋል የሚል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ470 ሺህ በላይ ሲሆን በበሽታው የተያዙት ደግሞ ከ9 ሚሊዮን አልፈዋል፡፡ ቫይረሱ በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ አህጉር በፍጥነት እየተዛመተ ሲሆን በተለይ ደቡብ አፍሪካ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎቿ በበሽታው መያዛቸው ሲታይ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *