loading
የዕርቀ ሰላም፣ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ሊቋቋም ነው

አርትስ 20/03/2011

 የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጆቹ ላይ የተነጋገረው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን እና የማንነትናየወሰን ኮሚሽን እንዲቋቋም ወስኖ እንዲፀድቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መላኩን ተከትሎ ነው ፡፡

በምክር ቤቱ ስብሰባ የዕርቀ ሰላም ኮሚሽንና የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ለማቋቋም በቀረበ ረቂቅአዋጅን ጨምሮ የፌደራል መንግስት አስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ማሻሻያተመልክቷል።

ከምክርቤቱ ስቡክ ገጽ ላይ እንዳገኘነዉ በምክር ቤት ውሎ ሁለቱ ኮሚሽኖችን ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይውይይት ካደረገ በኋላ ለውጭ ሰላምና ደህንናት እና ለህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ምልከታመርቶታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *