loading
የዚምባቡዌ የሰራተኛ ማህበራት መንግስትን  የምንታገሰው ለ48 ሰዓት ብቻ ነው አሉ፡፡

የዚምባቡዌ የሰራተኛ ማህበራት መንግስትን  የምንታገሰው ለ48 ሰዓት ብቻ ነው አሉ፡፡

ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ በምርጫ ወቅት የገቡትን ቃል ማክበር ተስኗቸው ከህዝባቸው የሚነሳው ጥያቄ ፋታ ነስቷቸዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በምርጫ ቅስቀሳቸው  ወቅት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሻሻል  ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም ወደ ስራው ሲገቡ ግን ፈተናው ቀላል አልሆነላቸውም፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው የመንግስት ሰራተኞች ማህበራት በ48 ሰዓታት ውስጥ የደሞዝ ማስተካከያ ካልተደረገልን ስራ አቁመን ለተቃውሞ አደባባይ እንወጣለን የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥተቸዋል፡፡

የምናንጋግዋ አስተዳደር በሀገሪቱ  በከሰተው የነዳጅ ዋጋ  ጭማሬ ሳቢያ  የተቃውሞ  ሰልፍ ባደረጉ ግለሰቦች ላይ ፖሊስ በወሰደው ያልተመጣጠነ እርምጃ ከባድ ወቀሳ እየደረሰበት ይገኛል፡፡

በሰልፈኞቹ እና በፖሊስ  መካከል ተፈጠረ በተባለው ግጭት 12 ሰዎች ተገድለዋል የሚል ወሬ ቢሰማም ፖሊስ ግን ሶስት ሰዎች ብቻ መሞታቸውን ተናግሯል፡፡

መንግስት ራሱ ያዋቀረው የሰብዓዊ መብት ተቋም ግን ፖሊስ  በሰልፈኞቹ ላይ ከመጠን በላይ ሀይል ተጠቅሟል ሲል ክስ አቅርቧል፡፡

በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በአመፁ ጀርባ አሉበት ተብለው በፖሊስ እየታደኑ ነው፡፡  ይህን የታዘቡ ወገኖች ደግሞ ዚምባቡዌ ወደ ሙጋቤ ዘመን ልትመለስ ነው በማለት ስጋታሰቸውን እየገለፁ  ይገኛሉ፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *