የዛምቢያው ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በፀረ ቻይና አቋማቸው ከፖሊስ ጥያቄ ቀረበባቸው
አርትስ 13/03/2011
የናሽናል ዴቨሎፕመንት ጥምረት ፓርቲ መሪ የሆኑት ሀኬንዴ ሂችሌማ የቻይናውያንን ፍላጎት ለማሟላት ሲባል የሀገሬው ህዝብ ጥቅም እየተጎዳ ነው የሚል አቋም አላቸው፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ሂችሌማ የዛምቢያ መንግስት የሚያስተዳድረው የጣውላ ፋብሪካ ለቻይና ኩባንያ ተሸጧል የሚል መግለጫ በመስጠታቸው በርካታ ህዝብ ለአመፅ ወደ ጎዳና ወጥቷል፡፡
ለተቃውሞ አደባባይ የወጡት ሰወች ደግሞ በቻይናውያን ንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ብሏል ፖሊስ ፡፡
ፖለቲከኛው ከፖሊስ ጣቢያ እንደተመለሱ ይህ ለዛምቢያ ህዝብ ጥቅም ሲባል የተከፈለ መስዋዕትነት ነው፤ የምንፈራ ከሆነ ህዝባዊ ስልጣንን ማሰብ የለብንም ብለዋል፡፡
በ2016 ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድረው በኤድጋር ሉንጉ የተሸነፉት ሂችሌማ አሁን ድረስ ውጤቱን እንደማይቀበሉት ደጋግመው ይናገራሉ፡፡
ሂቺሌማ ከፖሊስ ጣቢያ እንደተመለሱ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ይህ ለዛምቢያ ህዝብ ጥቅም ሲባል የተከፈለ መስዋእትነት ነው፤ የምንፈራ ከሆነ ህዝባዊ ስልጣንን ማሰብ የለብንም ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ኤድጋር ሉንጉ ዛምቢያን ማስተዳደር ከጀመሩ ወዲህ ሀገሪቱን ከፍተኛ የውጭ ዕዳ ውስጥ አስገብተዋታል ተብለው ይተቻሉ፡፡