loading
የዝውውር መስኮቱ  ለክረምቱ ጊዜ ቀጠሮ በመያዝ ትናንት ምሽት ዕኩለ ሌሊት ላይ ተዘግቷል፡፡

በጥር የተጫዋች የዝውውር መስኮት የመዝጊያ ዕለት በርካታ ክለቦች ተሳትፈዋል

የዝውውር መስኮቱ  ለክረምቱ ጊዜ ቀጠሮ በመያዝ ትናንት ምሽት ዕኩለ ሌሊት ላይ ተዘግቷል፡፡

በርካታ ተጫዋቾችም የነበሩበትን ክለብ ለቀው በውሰት ውል አዲስ ማረፊያ ቡድን ተቀላቅለዋል፡፡

የእንግሊዙ ኢቨርተን አማካዩን እድሪሳ ጉዬ ለፒ.ኤስ.ጂ አሳልፌ አልሰጥም ብሎ፤ በጉዳት በጣፋጮቹ ስኬታማ ጊዜን ማሳለፍ ያልቻለውን ያኒክ ቦላሴ ወደ ቤልጅየም አንደርሌክት በውሰት ውል አስከ ክረምት ማረፊያህ ይን ብሎ ሸኝቶታል፡፡

……………………………….

ስቶክ ከፕሪምየር ሊጉ ሲወርድ አብሮት የወረደው የቀድሞ የሊቨርፑል መለሎ ተጫዋች ፒተር ክሮች፤ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ዳግም በመመለስ እስከ የውድድር ዓመቱ ማብቂያ ድረስ በበርንሊ ለመቆየት ተስማምቷል፡፡ ሳም ቮክስ ደግሞ በርንሊን ለቆ ስቶክን ተቀላቅሏል፡፡

………………………………..

የለንደኑ ፉልሃም ተጫዋቹን አቡባካር ካማራን ወደ ቱርኩ ዬኒ ማላትያስፖር በውስት ውል መላኩን ተከትሎ፤ የሊቨርፑሉን ተጫዋች ላዛር ማርኮቪች በነፃ ዝውውር አስፈርሞታል፡፡

……………………………….

ጃፓናዊው ሽንጂ ካጋዋ የጀርመኑን ቦርሲያ ዶርትሙንድ ተሰናብቶ፤ የቱርኩን ቤሲክታስ በውሰት እስከ የውድድር ዓመቱ ማብቂያ ድረስ ተቀላቅሏል፡፡

……………………………….

ጋናዊው ሱሌ ሙንታሪ ባለፈው ክረምት ከዲፖርቲቮ ላ ካሮኛ ጋር ከተለያየ በኋላ ነፃ ተጫዋች የነበረ ሲሆን አሁን ወደ ስፔን ሁለተኛ ዲቪዥን አልባሴቴ ተዘዋውሯል፡፡

የ34 ዓመቱ አማካይ ከዚህ ቀደም ፖርትስመዝ፣ ሰንደርላንድ እንዲሁም በጣሊያን ቆይታው ኢንተርና ኤስ ሚላን ተጫውቶ አሳልፏል፡፡

……………………………….

የእንግሊዙ ኒውካስትል ዩናይትድ ደግሞ የዝውውር ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት የክለቡን የተጫዋቾች የዝውውር ክብረወሰን በሰበረ መንገድ ፓራጓያዊውን ሚጉዌል አልሚሮን በ20 ሚሊየን ፓውንድ ሂሳብ ከአሜሪካው አትላንታ ዩናይትድ ተቀላቅሏል፡፡ የሞናኮውን አንቶኒዮ ባሬካ ደግሞ በውሰት ውል አስፈርሞታል፡፡

……………………………….

ቼልሲዎች በውሰት ውል በተደጋጋሚ ለተለያዩ ክለቦች የሚሰጡትን ቤልጂየማዊ ሚኪ ባትሹዬ የቶተንሃምን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ወደ ሌላኛው የለንደን ክለብ ክሪስታል ፓላስ በውሰት ሸኝቶታል፡፡

……………………………….

ሌስተር ሲቲ ደግሞ የሞናኮውን ዮሪ ቴሊማንስ ከሞናኮ በውሰት ያስፈረመ ሲሆን በምትኩ አንድሬን ሲልቫን ወደ ፈረንሳዩ ክለብ ሸኝቶታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *