loading
የዩኒቨርቲዎች ስትራቴጂክ ዕቅድ ግምገማ መድርክ እየተካሄደ ነው::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 የዩኒቨርቲዎች ስትራቴጂክ ዕቅድ ግምገማ መድርክ እየተካሄደ ነው:: የዩኒቨርቲዎች ስትራቴጂክ ዕቅድ ግምገማ መድርክ እየተካሄደ እንደሚገኝ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቀ፡፡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ
እንደገለጹት፣የትምህርት ስርዓታችንን በተለመደው መልኩ የምንመራው ሳይሆን ብቁና ጥራት ያለው ዜጋ ለማፍራት በስትራቴጂክ ዕቅዳችን በማካተት የትምህርት ተቋማት በግልጽ ማቀድና መተግበር ይኖርባቸዋል፡፡

በሀገር ደረጃ በተዘጋጀው የአስር ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የገለጹት ሚኒስትሩ ባቀድነዉ ልክ ሁሉም የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ ካደረገ ከድህነት ወጥተን ወደ ብልጽግና ጉዞ የሚወስደን ይሆናል ብለዋል፡፡ የተሻለ ዕቅድ ላቀረበ ዩኒቨርሲቲ እዉቅና እየሰጠን መሻሻል ያለበት ዕቅድ ማሻሻያ እየተደረገበት የሚዳብር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እስካሁን የምንጠቀምበት የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ፣ እስትራቴጂና ፕሮግራም በ1986 ዓ.ም የተዘጋጀዉ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ነው፡፡

ፖሊሲው ያሳካቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆኖ እንዴት አድርገን ሁለንተናዊ የሀገሪቱን ብልጽግና እናሳካለን ለሚለው ብዙ ጥናቶች ተደርገዋል ብለዋል፡፡ ጥናቱን ተከትሎ የሀገሪቱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቷል ከፍኖተካርታዉ ዝክረ ሀሳብ በመነሳትም የፖሊሲ ማሻሻያ መደረግ እንዳለበት አመላካች ጉዳዮች መኖራቸዉን ጠቅሰዋል፡፡ በሪፎርም ስራችን የበለጠ ትኩረት የተሠጣቸዉን የግብርና፣ማኑፋክቸሪግ ኢንዱስትሪ፣ማዕድን፣አይሲቲ እና ቱሪዝምን ማዕከል ያደረጉ ብቁ ምሩቃንን በማፍራት ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር በማድረግ የኢኮኖሚ ስብራቱና የምርታማነት ማነስ የሚቀርፍ ስልት ያካተተ እስትራቴጂክ ዕቅድ መሆን ይጠቅበታል ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *