loading
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሩሲያን በመቃወም ከጎናቸው እንዲቆም ዳግም ጥሪ አሰተላለፉ::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሩሲያን በመቃወም ከጎናቸው እንዲቆም ዳግም ጥሪ አሰተላለፉ:: ሩሲያ የዩክሬንን ድንበር ጥሳ በመግባት ጦርነት ከከፈተች ድፍን አንድ ወር ያስቆጠረች ሲሆን እስካሁን በጦርነቱ ሳቢያ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዩክሬናዊያን ሀገራቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በቴሌግራም ገጻቸው ባስታላለፉት መልእክት ዩክሬንን መደገፍ ነጻነትን መደገፍ ነው እናም መላው ዓለም ከእኛ ጎን ለመቆም ጊዜው አሁን ነው ብለዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤም በዩክሬን የደረሰውን ሰብዓዊ ቀውስ ተከትሎ በሩሲያ ላይ አዲስ ውሳኔ ለማሳለፍ መዘጋጀቱን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡


የቡድን ሰባት አባል ሀገራት በጦርነቱ ዙሪያ ለመምከር የተሰባሰቡ ሲሆን ይሄኛው ስብሰባ እንደተጠናቀቀ የኔቶ አባላት ስብሰባም ይቀጥላል ተብሏል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለፑቲን መልዕክት ለማስተላለፍ ብራሰልስ መግባታቸው ተሰምቷል፡፡ ባይደን በቡድን ሰባትና በኔቶ ስብሰባ ወቅት የምእራባዊያን አጋርነትና ጥምረት በቀዝቃዛው ጦርነት መጨረሻ ከነበረው የበለጠ ጠንካራ እንደሆነ ለፑቲን እንነግራቸዋለን ብለዋል፡፡ ሞስኮ በበኩሏ የሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት በቋፍ ላይ እንደሚገኝ በመግለጽ ዋሽንግተን አቋሟን ካላስተካከለች ያልተጠበቀ ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቃለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *