loading
የዩጋንዳ ፖሊስ የፓርላማ አባሉን ለህክምና ወደ ውጭ እንዳይሄዱ ከልክሏቸዋል፡፡

አጃንስ ፍራንሰ ፕሬስ እንደዘገበው ፍራንሲስ ዛክ የተባሉት የፓርላማ አባል በደረሰባቸው የመቁሰል አደጋ ሳቢያ ህክምና ፍለጋ ወደህንድ ሊጓዙ ሲሉ ከኢንተቤ አየር ማረፊያ በጸጥታ ሰራተኞች ታግደዋል፡፡
የአየር መንገዱ የደህንነት ሰዎች ስለሁኔታው ተጠይቀው በሰጡት መልስ ፖሊስ በሳቸው ዙሪያ ማጣራት የሚፈልገው ጉዳይ ስላለው ለሱ መልስ ሳይሰጡ ወደ የትኛውም የውጭ ሀገር ጉዞ ማድረግ አይችሉም ብለዋል፡፡
ዛክ ባለፈው ወር በፕሬዝዳንት የዌሬ ሙሴቬኒ ተሸካርካሪ ላይ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ጥርጣሬ በፖሊስ ተይዘው እስር ቤት ገብተው ነበር፡፡
በመሆኑም በፖሊስ ሲያዙና እስር ቤት በገቡበት ወቅት በደረሰባቸው ድብደባ ሳይሆን አይቀርም የቆሰሉት ይላሉ ደጋፊዎቻቸው፡፡
የዩጋንዳ መንግስት ቃል አቀባይ ዛክ በህክምና ሰበብ ከህግ ለማምለጥ እየሞከረ ስለሆነ መታሰር አለበት የሚል ጽሁፍ በቱይተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
ይሁን እንጂ የዛክ ጠበቃ ደንበኛዬ ምንም ዓይነት ክስ ስላልተመሰረተባቸው ውጭ ሀገር ሄደው ለመታከም ከፖሊስ የምስክር ወረቀት አያስፈልጋቸውም ብለዋል፡፡

አርትስ 25/12/2010

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *