የደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጥሪ አቀረቡ
የደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጥሪ አቀረቡ
ርትስ 22/02/2011
ፕሬዝዳንቷ ለደቡብ ሱዳን ሰላም ማብሰሪያ ፕሮግራም ላይ በመታደም በጁባ በጆን ጋራንግ አደባባይ ባደረጉት ንግግር ተፈራራሚ ወገኖችንና የደቡብ ሱዳን ህዝብን እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ፤ የሽግግር ተቋም ኮሚቴ ቶሎ በማቋቋም ከቅድመ ሽግግር ሰራዎች ቶሎ ወደ ሽግግር መንግሰቱ መቋቋም መገባት አለበት ብለዋል፡፡
ባለፈዉ አመት መስከረም ወር በአዲስ አበባ በኢጋድ አደራዳሪነት በፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና በዶክተር ሪክ ማቻር መካል የተደረሰዉን የሽግግር መንግስት ማቋቋም የሰላም ስምምነትከተፈረመ በኋላበደቡብ ሱዳን ግጭት እየቀነሰ መምጣቱ ተነግሯል፡፡