የደቡብ አፍሪካ የሀገር ዉስጥ ሚኒስትር ከፓርላማ አባልነት ራሳቸውን አገለሉ
አርትስ/03/2011
ባለፈው ማክሰኞ ከሚኒስትርነታቸው የለቀቁት ማሉሲ ጊጋባ ከፓርላማ አባልነታቸውም በገዛ
ፈቃዳቸው ተሰናብተዋል፡፡
ሮይተርሰ እንደዘገበው ጊጋባ ከሚኒስትርነታቸው የለቀቁት በኢሚግሬሽን አሰራር ላይ ባልተገባ መንገድ
የግል ጥቅማችውን ሲያሳድዱ ተደርሶባቸው ነው፡፡
የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ሚኒስትሩ ሲሾሙ በቃለ መሃላ የገቡትን ህዝብን በታማኝነት
የማገልገል ቃል አፍርሰው መገኘታቸውን ገልጿል፡፡
በፈረንጆቹ ከ2017 እስከ 2018 የፋይናንስ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ጊጋባ፤ ህግን የሚፃረር
ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ውስጥ እንዳልተሰተፉ ተናግረዋል፡፡