የጋራ ንቅናቄ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ መስራች አቶ ኦባንግ ሜቶ ከ16 ዓመታት ቆይታ በኋለ ጋምቤላ ገቡ
አርትስ 07/01/2010 ዓ.ም
በጋምቤላ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሰናይ አኳርን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
አቶ አቦንግ በአቀባበሉ ላይ እንደተናገሩት ትግላችን ለአንድ ብሄር ነፃነት ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያ ነፃነት ነው ብለዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሰናይ አኳር በበኩላቸው ንቅናቄው መንግስት ያላያቸውን ክፍተቶች በማሳየት የሰብአዊ መብት እንዲከበር ለሚያደርገው እንቅስቃሴም ሆነ ለአጠቃላይ ዓላማው ስኬት ክልሉ የበኩሉን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
አቶ ኦባንግ በቆይታቸው በክልሉ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ አካለት ጋር ውይይት ያደርጋሉ።