loading
የጤናውን ዘርፍ ጥራት እና ተደራሽነት ለማሳደግ የግሉ ዘርፍ እየተጫወተ ያለው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 የጤናውን ዘርፍ ጥራት እና ተደራሽነት ለማሳደግ የግሉ ዘርፍ እየተጫወተ ያለው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ::የጤና ጥበቃ ሚንስተር ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ ለጤናው ዘርፍ መንግስት ከሰጠው ትኩረት ጎን ለጎን የግሉ ዘርፍ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ዶክተር እመቤት ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ አሁን ላይ በአለማችን የጥርስ ህክምና የመጨረሻ ቴክኖሎጂ የሆነውን ካድ ካም የተሰኘውን ማሽን ወደ ሀገራችን አስገብቷል፤ይህ ቴክኖሎጂ ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ መልኩ በቀን ከ200 – 300 ምትክ ጥርሶችን ማምረት እንደሚችል ተነግሯል።

የጤና ጥበቃ ሚንስትሯ ዶክተር ሊያ ይህ ቴክኖሎጂ በአለማችን በጥርስ ህክምና የመጨረሻ ደረጃ የደረሰ ቴክኖሎጂ ከመሆኑ አንፃር እንደ ሀገር የህክምና ቱሪዝምን ለማስፋፋት የላቀ ሚና ይጫወታል ብለዋል።መንግስት በጤናው ዘርፍ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት የግሉን ሴክተር ተሳትፎ እና አጋርነት በማጠናከር እንድሚሰራ ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

በህክምና ዘርፉ የስራ እድል ከመፍጠር አንፃር የግሉ ሴክተር እያደረገ ያለው ጥረት ተጣናክሮ መቀጠል እንዳለብት ነዉ የገለፁት፡፡ሚኒስትሯ ቴክኖሎጂውን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የጤናውን ዘርፍ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚደረገው ጥረት የሚበረታታ ነው ብለዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *