loading
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለመቄዶንያ የአምቡላንስ እርዳታ አደረገ

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለመቄዶንያ የአምቡላንስ እርዳታ አደረገ

አርትስ 30/02/2011

በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እስክንድር ላቀው መቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማእከል ተገኝተው አምቡላንሶቹን ባሰረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ፤ማዕከሉ የጤና ጥበቃ ስራን በማገዝ ላይ ስለሚገኝ መስሪያ ቤቱ አቅም በፈቀደው ሁሉ ከእርዳታ ማእከሉ ጎን እንደሚቆም ተናግረዋል፡፡

የሀብትና ንብረት ቁምነገር የሚለካው በተሰበሰበው መጠን ሳይሆን ለጥሩ ነገር በዋለው ልክ ነው ያሉት አቶ እስክንድር፤ ሁሉም አካላት የተቻላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

አቶ እስክንድር ጨምረው እንደተናገሩት የነገውን ስለማናውቅ በጎ መስራት ከሁላችንም ይጠበቃል ብለው የማዕከሉ መስራች ዶ/ር ቢንያም በለጠ ከእሳቸው በላይ አቅም ያላቸው አካላት ያላደረጉትን ማድረግ በመቻላቸው ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ይህ እርዳታ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሲደረግ የመጀመሪያው አይደለም ያሉት የማዕከሉ መስራች ቢንያም በለጠ ፤መስሪያ ቤቱ ከአሁን በፊትም የተለያዩ ልገሳዎችን በማድረግ ማዕከሉን ሲረዳ መቆየቱንና፤ ለማዕከሉ ክሊኒክ የጤና ባለሙያዎችን በመመደብ ተረጂዎቹ በማዕከሉ ውስጥ የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ አስችሏል ብለዋል፡፡

ለማዕከሉ የተበረከቱ አምቡላንሶች ሁለት ሲሆኑ በገንዘብ ከሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ ናቸው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *