loading
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ተሸላሚ ሆኑ

የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ተሸላሚ ሆኑ

አርትስ 05/04/2011

 ሽልማቱ በዩኒቨርሲቲው በሚዘጋጀውና በጤና ዘርፍ የአመራርነትና በጎ አስተዋጽኦ አበርክቶ ዘርፍ ላይ የሚሰጥ ሲሆን፥ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ  ዶክተር አሚር አማንም የ2018 ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

ከሚኒስቴሩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ እንደተገኘው መረጃ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዌስተርን ኬፕ  ዶክተር አሚር አማን በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ላይ እየፈጠሩ ባሉት ተጽዕኖ ነው የሸለምኳቸው ብሏል፡፡

ሚኒስትሩ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስላበረከተላቸው ሽልማት በፌስ ቡክ ገጻቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዩኒቨርስቲው በደቡብ አፍሪካና በተለያዩ ሀገራት በጤናው ዘርፍ ትምህርት በመስጠት እንዲሁም በምርምር ስራዎች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ተቋም ነው፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *