loading
የጥምቀትን በዓል በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።

የጥምቀትን በዓል በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

የባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከብሮ የሚውለውን  የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።

የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ካሳሁን አያሌው እንደተናገሩት ከማይዳሰሱ ቅርሶች የሚመደበውን የጥምቀትን በዓል

ወደ ቱሪስት መስህብነት ለመለወጥ ከወረዳዎች ጀምሮ እስከ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ድረስ ጥረት እየተደረገ ነው።

በሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮራ፣ በደቡብ ክልል ደራሼ፣ በትግራይ ክልል ማይጨው እና ሌሎች አካባቢዎች የበዓል አከባበሩን የማስተዋወቅ እና ጎብኝዎች እንዲታደሙ ሁኔታዎችን የማመቻቸት ሥራዎች መሠራታቸውንም ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡

በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት መመዝገቡ በዓሉ ዓለም አቀፍ ዕውቅናው እንዲጨምር እና የጎብኝዎች ፍሰት ከፍ እንዲል ይረዳልም ነው ያሉት ባለሙያው፡፡

የጥምቀት በዓል ለቱሪዝሙ ዘርፍ ከፍተኛ ፋይዳ አለው ያሉት አቶ ካሳሁን ሃይማኖታዊ ይዘቱን እና ፌስቲቫሎችን እንዲሁም ትዕይንቶችን ለመታደም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጎብኝዎች እንደሚመጡም ነው የተናገሩት፡፡

ይህም ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ጠቀሜታ ያበረክታል ፣ የአማራ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገበው፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *