loading
የፈረንሳያዊው ኦስማን ዴምቤሌ የባርሳ ቆይታ በቅርቡ ያከትም ይሆን?

አርትስ ስፖርት 10/03/2011

በውዝግብ የተሞላ የዝውውር ሂደትን አሳልፎ ከቦርሲያ ዶርትሙንድ ወደ ባርሴሎና ያቀናው ፈረንሳያዊው ወጣት ተጫዋች ኦስማን ዴምቤሌ፤ በካታላን በአጭር ጊዜ ቆይታውም ደስ የማይል ወቅት  እያሳለፈ ይገኛል፡፡

ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ይህን ተጫዋች ለማዛወር የሰሜን ለንደኑ አርሰናል አይኑን ያሳረፈ ሲሆን እንዳውም ጫፍ ላይ እንደደረሰ እየተነገረ ይገኛል፡፡ ከእግር ኳስ ህይወቱ ወጣ ብሎየሚያከናውናቸው ተግባራት የካታላኑን ክለብ በተጫዋቹ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥና ለሌላ ክለብ አሳልፎ እንዲሰጥ እንዳስገደደው እየተነገረ ይገኛል፤ ከወዲሁም የተጫዋቹ ተተኪ ይሆናሉ ተብለው ከታሰቡተጫዋቾች መካከል የቀድሞ የክለቡ አባል ኔይማር፣ ኤደን ሀዛርድ፣ አንቶኒ ማርሲያል፣ ሜምፊስ ዲፓይ እና ፓውሎ ዲባላ ይገኙበታል ሲል ዘ ሰን አስነብቧል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *