loading
የፈረንሳይና የኢትዮጵያ ግንኙነት እያደገ መምጣቱን በፈረንሳይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደር ተናገሩ፡፡

የፈረንሳይና የኢትዮጵያ ግንኙነት እያደገ መምጣቱን በፈረንሳይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደር ተናገሩ፡፡

አምባሳደር ሄኖክ በፈረንሳይ ከሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ጋር  ባደረጉት ዉይይት የፈረንሳይና የኢትዮጵያ ግንኙነት እያደገ መጥቷል  በቅርቡም የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝትም ለዚህ አይነተኛ ማሳያ ነው ብለዋል።

አምባሳደሩ በነበራቸዉ ወይይትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ የተገኙ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለዉጦች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።

መንግስት በሁሉም ዘርፎች በተለይም አጠቃላይ አገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ ሁሉን አቀፍ ጥረት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ኤምባሲው በፈረንሳይና ውክልና በተሰጠባቸው አገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ አባላት አስፈላጊውን ግልጋሎት ለመስጠት ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

ምንጭ፤-ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃላቀባይ ጽ/ቤት

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *