loading
የፈረንሳይ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ያለዉን የመገናኛ ብዙሃን አቅምን ለማሳደግ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክርቤት ጋር ድጋፍ ለማድረግና በጋራ ለመስራት ተስማሙ ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013 የፈረንሳይ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ያለዉን የመገናኛ ብዙሃን አቅምን ለማሳደግ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክርቤት ጋር ድጋፍ ለማድረግና በጋራ ለመስራት ተስማሙ ፡፡

ድጋፉ በተለይም የሚዲያ ነፃነት የሙያዉን ስነምግባር ባከበረ መልኩ እንዲሆንና በዘርፉ ላይ ባለሙያዎችን እንዲሁም የሚዲያ ተቋማትን ለማሰልጠን እንደሚዉልና አይነተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረዉ ተገልጿል፡፡የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በዋናነት የሚዲያ ነፃነት ላይ በኢትዮጵያ ያሉ የመገናኛ ቡዙኃን በትክክል ሀላፌነታቸዉን እንዲወጡ ማድረግ እንዲሁም በስነምግባር የታነፁ ብሎም ሃላፌነት የሚሰማቸዉ ለማድረግ እንደሚሰራ የገለፁት የምክር ቤቱ ሊቀመንበር አቶ አማረ አረጋዊ የፈረንሳይ መንግስት በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትንና ለማረጋገጥና በትክክል ሀላፌነታቸዉን እንዲወጡ ለማድረግ እንዲቻል እየሰጠ ያለዉ ድጋፍ ወቅቱንና ጊዜዉን ያገናዘበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር በበኩላቸዉ የኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ ጋዜጣ የታተመዉ በፈረንሳይ ዉስጥ መሆኑን ገልፀዉ፤ በዘርፉ ላይ በጋራ ለመስራትና ድጋፍ ለማድረግ የፈረንሳይ መንግስት ያለዉን ተነሳሽነት ገልፀዋል፡፤የመገናኛ ብዙሃን ሚና ሀገርን ለመገንባት አይነተኛ ሚና ቢኖረዉም፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ ይሕ ሊሆንበት ያልቻለበት ምክንያትም በመድረኩ ተነስትዋል፡፡በፈረንሳይ መንግስት የተደረገዉ ድጋፍ በዘርፉ ላይ ስልጠና ለመስጠትና አቅም ለማሳደግ ይዉላል ተብሏል ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *