loading
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ ህጎችን የማርቀቅና የማሻሻል ስራ እየተሰራ ነው አለ

አርትስ 04/03/2011

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ  ሰሞኑን በቁጥጥር ስር በዋሉ ሰዎችና በፍትህ ስርዓቱ ማሻሻያ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ላይ  ባለፉት ስድስት ወራት በፍትህ ስርዓቱ ላይ በርካታ ስራዎች መሰራታቸው የተነገረ ሲሆን የበጎ አድራጎት ማህበራት ረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ፣  የሽብርተኝነት ህግ ረቂቅአዋጅ ላይ፣ የወንጀል ስርዓት ላይ፣ የንግድ ህግ እና የሚዲያ ህግ ማዕቀፍ ሂደት ላይ፣ የምርጫ እናየፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅላይ መሰራቱን ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ተናግረዋል፡፡

ከእነዚህ ማሻሻያዎች ውስጥ የበጎአድራጎት ረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ በቀጣዩ ሳምንት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ይመራል ተብሏል፡፡

አቶ ብርሃኑ የሽብርተኝነት ህጉ ረቂቅ አልቆ  ውይይት እየተደረገበት መሆኑን እና የወንጀል ስርዓት፣ የንግድ ህግ እና የሚዲያ ህግማዕቀፍ በሂደት ላይ እንደሆኑ፥ የምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅን በሚመለከትም ምክክር እየተደረገ እንደሆነ ነው የገለፁት፡፡

ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ባለፉት ስድስት ወራት ተከናውነዋል ካሏቸው ስራዎች መካከል  በርካታ ታራሚዎች በምህረትና በይቅርታመለቀቃቸው የሚጠቀስ ነው ብለዋል፡፡

ባለፉት ወራት ከሙስና እና ሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ  በተደረገ ምርመራም በተለይም በሶማሌ፣ አዲስ አበባ እና በቤኒሻንጉልለተፈጸሙ ጥቃቶች  የማጣራትና ተጠርጣሪዎችን የመለየት ስራ ተደርጓል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *