የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ- ህግ የሰኔ 16ቱ የአዲስ አበባው የቦምብ ጥቃት በመረጃና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ሀላፊ የተመራ ነው አለ
አርትስ 03/ 03/2011
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫው እስካሁን በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል 36 ተጠርጣሪዎች ፤27 ቱ በሙስና በቁጥጥር ስር መዋላቸው እና ሰባት ድብቅ እስር ቤቶች በአዲስ አበባ ተገኝተዋል ብሏል።
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን በተመለከተ፦
ከ2004 እስከ 2010 ድረስ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን 37 ቢሊየን ብር የውጭ ግዢ ፈፅሟል።
እነዚህ ግዢዎች ዓለም አቀፍ ጨረታ ሳይፈፀምባቸው የተከናወኑ ናቸው።
ግዢዎቹ በጥቅም በተሳሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት መካከል እና በደላላ የተከናወነ መሆኑ ታዉቅዋል ።
በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ላይ ከፍተኛ የሚባል የሰብዓዊ መብት ጥሰት ደርሷል እንደ ጠቅላይ አቃቤ ህግ መግለጫ፡፡
ወንጀል መፈፀም የሚጀምሩት ወደ ህግ አካል ሳይቀርቡ እንደሆነ የሚያትተው መግለጫው ወንጀሎች በዋናነት የሚመሩት በደህንነት አመራሮች እንደሆነ አሳውቋል፡፡
በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወቅት የአካል የስነ ልቦናና ማህበራዊ ህይወት መቃወስ ደርሷል፡፡ ጥቃቶቹ ዘርን መሰረት የደረጉና የተጠርጣሪ ቤተሰብን እስከማሳደድና ነፃነት እስከማሳጣት የሚደርስ ነበር ተብሏል፡፡
ችግሮቹ ከተፈጠሩ ቆይተዋል ያሉት ፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ በህግ ቁጥጥር ስር ያልዋሉ ተጠርጣሪዎች እንዳሉና በቀጣይ እነሱን የመያዝ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በአገር ውስጥ ግዥም አጋር ናቸው በማለት ከኮርፖሬሽኑ ጋር ዝምድና ካላቸው ሰዎች ላይ ግዥ ሲፈጸም ቆይቷል፤ በዚህም ከአንደ ድርጅት ለ21 ጊዜ ከሌላ ድርጅት 15 ጊዜና 18 ጊዜ ተደጋጋሚ ግዥዎች ተፈጽመዋል፤
ግዢዎቹ በጥቅም በተሳሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት መካከል እንዲሁም በደላላዎች የተከናወኑ ናቸው።
ተቋሙ በፈፀማቸው ትላልቅ ግዢዎች ላይ ምርመራ ተካሂዷል ከተልኮ ውጭ የተፈፀሙ የመርከብ እና የአውሮፕላን ግዢዎች ይገኙበታል።