የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እና የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ሀላፊ አቶ ያሬድ ዘሪሁን በቁጥጥር ስር ዋሉ
አርትስ 06/03/2011
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለአርትስ እንደገለፀው ተጠርጣሪው በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ውለዋል።
አቶ ያሬድ ዘሪሁንን አስመልጠዋል በሚል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ትናንት ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል፡፡
ከነዚህ ግለሰቦች መካከል የነብስ አባቱ አባ ሃይለማርያም ሃይለሚካኤል እና ሾፌራቸው አሸናፊ ታደለ ናቸው ፍርድቤት የቀረቡት፡፡