loading
የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል ዘርፉን በእውቀት መምራት ያስፈልጋል- ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22፣ 2013 የፍርድ አፈፃፀም መጓተት ችግሮችን ለመፍታት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራር መተግበር ይገባል ተባለ፡፡ የፌዴራል የፍትህ የህግ ምርምር እና ሥልጠና ኢንስቲትዩት ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዲስ አበባ አውደ-ጥናት አካሂዷል። በአውደ-ጥናቱ ላይ  ከፍርድ አፈፃፀም ጋር ያሉ ችግሮች፣ ከአዕምሮ ጤና ህግ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች እንዲሁም ባህላዊ የግጭት አፈታት ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል። የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በዚህን ወቅት የህግና ፍትህ ሥርዓቱን ለማሻሻል ሥራውን በእውቀት፣ በመረጃ እና በጥናት ላይ ተመስርቶ መምራት ይገባል ብለዋል። የፌዴራል የፍትህና የህግ ምርምር እና ሥልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በበኩላቸው የፍርድ አፈፃፀም መጓተቶች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እየፈጠሩ መጥተዋል ነው ያሉት።

ተቋማቸው በተሰጠው ተልዕኮ መሰረት ችግሩን ለመፍታት መፍትሔ አመላካች ጥናት ማድረጉንም ተናግረዋል። የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ማዳ  የፍርድ ግብ ውሳኔ መስጠት ብቻ ሳይሆን  የተሰጠውን ውሳኔ ማስፈጸም ጭምር ነው ብለዋል። የፍርድ ውሳኔ ማስፈጸም ከዜጎች መብት ጋር እንደሚያያዝም  ገልጸው፤ የፍርድ አፈፃፀም መጓተት ምክንያት የሆኑ የአደረጃጀት እና የአሠራር ችግሮች መፈታት አለባቸው ብለዋል። ይህን ለማድረግ ደግሞ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር በመዘርጋት ችግሩን መቅረፍ እንደሚቻልም ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *