loading
የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልጅ ባሮን ትራምፕ በኮሮናቫይረስ መያዙ ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2013 የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልጅ ባሮን ትራምፕ በኮሮናቫይረስ መያዙ ተሰማ:: ከሁለት ሳምንት በፊት ከባለቤታቸው ጋር ጋር በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ማቆያ የሰነበቱት ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ የልጃቸውን በበሽታው መያዝ ይፋ አድርገዋል፡፡ የ14 ዓመቱ ባሮን ትራምፕ ተመርምሮ የመጀመሪያ ውጤቱ ኔጌቲቨ እንደነበር የገለፁት ቀዳማዊት እመቤቷ እኔና ባለቤቴ በበሽታው መያዛችንን ሳውቅ ስለልጃችን አብዝቸ ስጨነቅ ነበር ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ስለባሮን ጤንነት ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ በመልካም ሁኔታ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ትራምፕ አያይዘውም ባሮን ወጣት በመሆኑ ፈጥኖ የማገገም ችሎታው ከፍተኛ ነው በቫይረሱ እንደተያዘ እንኳን ያወቀ አልመሰለኝም ምክንያቱም ምንም አይነት ምልክት አልታየበትም ነበር ብለዋል፡፡ ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው ትራምፕ አሁን ስለበሽታው በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የአቋም ለውጥ የማሳየት አዝማሚያ ታይቶባቸዋል፡፡

ለዚህ ማሳያው ከአሁን ቀደም ሲያደርጉት እንደነበረው በበሽታው ማሾፍና መሳለቃቸውን ትተው ለታመሙና የቅርብ ሰዎቻቸውን በቫይረሱ ላጡ ሰዎች የሀዘን ስሜት ማሳየታቸው ነው ብሏል ዘገባው አክሎ፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም በደጋፊዎቻቸው ፊት ቀርበው ሲናገሩ ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ማገገማቸውን በኩራት መናገራቸውን አላቆሙም ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *