loading
የ10ኛው Globe Soccer ሽልማት እጩዎች ተለይተዋል

አርትስ ስፖርት 17/03/2011

Globe Soccer Awards ዘንድሮ ለ10ኛ ጊዜ የሚሰናዳ ሲሆን በአሰልጠኞች፣ በተጫዋቾች፣ በወኪሎች ተፎካካሪ እጩዎች ተለይተው ታውቀዋል፡፡

በዚህም በምርጥ ተጫዋችነት ሶስት ተጫዋቾች እጩ ሲሆኑ የቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ፤ የዓለም እና የኢሮፓ ሊግ ዋንጫ ባለድሉ አንቱዋን ግሪዝማን እና የዓለም ሻምፒዮኑ ክልያን ምባፔ ቀርበዋል፡፡

የዓመቱ ምርጥ ክለብ ክብርን ለመቀዳጀት በእጩነት የአውሮፓ ቻምፒንስ ሊግ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ እና የፍፃሜ ተፋላሚው የእንግሊዙ ሊቨርፑል እንዲሁም የኢሮፓ ሊጉ አሸናፊው አትሌቲኮ ማድሪድ በዕጩነትቀርበዋል፡፡

በአሰልጣኞች ባለፈው የውድድር ወቅት ለማድሪድ ስኬታማነት ዚነዲን ዚዳን፤ ለሊቨርፑል የርገን ክሎፕ፤ ለአትሌቲኮ ደግሞ ዲያጎ ሲሞኔ ተጠቃሽ በመሆናቸው በእጩነት ቀርበዋል፡፡ በተጨማሪም የዓለም ዋንጫንከፈረንሳይ ጋር ያነሱት ዲዲዬ ዴሾ፤ የዩቬንቱስ አሰልጣኝ ማሲሚሊያኖ አሌግሪ ተፎካካሪ ሆነው ቀርበዋል፡፡

ሽልማቱ የዓመቱ ምርጥ ወኪልነትንም ያካተተ ሲሆን ሆርሄ ሜንዴዝ ከ ጌስቲፉት፣ ጆናታን ባርኔት ከ ስቴላር ግሩፕ እንዲሁም ስቴፋኖ ካስታኛ ከ ፉትቦል ካፒታል ተካትተዋል፡፡

ሽልማቱ በአውሮፓ የተጫዋቾች ወኪል ማህበርና በአውሮፓ ክለቦች ማህበር የሚዘጋጅ፤ በየዓመቱ በእግር ኳስ ምርጥ የተባሉ የሚሸለሙበት ሲሆን የዘንድሮው ጥር 3/2019 በዱባይ ይከናወናል ሲል All Football አስነብቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *