loading
የ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ጀምሮ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ይቀጥላሉ፡፡

የ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ጀምሮ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ይቀጥላሉ፡፡

በፖርቱጋሉ ማርኮ ሲልቫ የሚመራው የመርሲ ሳይዱ ክለብ ኤቨርተን በጉዲሰን ፓርክ የሲን ዳይቹን በርንሊ ምሽት 4፡00 ላይ ይደረጋል፡፡

በነገው ዕለት ደግሞ አምስት ያህል ግጥሚያዎች ሲደረጉ፤ ቀን 8፡30 ቦርንመዝ በዲን ኮርት የማውሪሲዮ ፖቼቲኖውን ቶተንሃም ሆተስፐርን ያስተናግዳል፡፡   ስፐርሶች አሁንም የቀጣይ ዓመት የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፏቸውን ባለማረጋገጣቸው ጨዋታው ላይ ድልን አጥብቀው ይሻሉ፡፡

አመሻሽ 11፡00 ሰዓት ላይ ደግሞ በተመሳሳይ ሰዓት ዌስት ሃም ዩናይትድ በለንደን ስታዲየም ከሳውዛምፕተን፤ ወልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ በሞሊኒክ ስታዲየም ከሊጉ ከተሰናበተው ፉልሃም ጋር ይፋለማሉ፡፡

ምሽት 1፡30 ላይ ከሊጉ ላለመውረድ በቋፍ ላይ የሚገኘው የዌልሱ ካርዲፍ ሲቲ በሜዳው ከለንደኑ ክሪስታል ፓላስ ይጫወታል፡፡

4፡45 ሲል ደግሞ ሊቨርፑል ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ አምርቶ ከኒውካስትል ዩናይትድ ጋር ተጠባቂ ግጥሚያ ያደርጋል፡፡ የማግቢሶቹ አሰልጣኝ ስፔናዊው ራፋኤል ቤኒቲዝ ለቀድሞ ቡድናቸው ውለታ ይውሉ ይሆን የሚለው ይጠበቃል፡፡

ቀያዮቹ ድል የዕነርሱ የሚሆን ከሆነ ማንችስተር ሲቲ ጨዋታውን ሰኞ ምሽት እስኪጫወት ድረስ በሊጉ አናት ላይ ይቀመጣሉ፡፡

ዕሁድ ሶስት ግጥሚያዎች ሲደረጉ ቼልሲ ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ ጠንካራውን ዋትፎርድ 10፡00 ሰዓት ሲል ያስተናግዳል፡፡

ቀጣይ ዓመት የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን በጥብቅ ከሚፈልጉት ክለቦች አንዱ የሆኑት ሰማያዊዎቹ ከሃቪ ጋርሽያ ቡድን በኩል ቀላል የማይባል ፈተና ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡

የኦሌ ጉናር ሶልሻዬሩ ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ጆን ስሚዝ ተጉዞ ከሊጉ የተሰናበተውን ሀደርስፊልድ ታውን ይገጥማል፡፡ ከቶተንሃም፣ ቼልሲ እና አርሰናል ያነሰ የቻምፒዮንስ ሊግ ተስፋ ያላቸው ቀያይ ሰይጣኖቹ ቀሪ ጨዋታዎችን በድል በመወጣት የሌሎቹን ነጥብ መጣል ይጠብቃል፡፡

አርሰናል ምሽት 12፡30 በኤመሬትስ ስታዲየም ከሊጉ ላለመውረድ እየተፍጨረጨረ የሚገኘውን ብራይተን ይገጥማል፡፡ የኡናይ ኢመሪው ቡድን የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳፎውን ከዩሮፓ ሊጉ በበለጠ በዚህ ውድድር ላይ የማግኘት ፍላጎት ያላቸው በመሆኑ ትኩረት ተስጥቶታል፡፡  

የፔፕ ጓርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ በሜዳው ኢቲሃድ ስታዲየም የብሬንዳን ሮጀርሱን ሌስተር ሲቲ ያስተናግዳል፡፡ ሌስተር ባለፈው ሳምንት አርሰናልን ሳይጠበቅ ጉድ የሰራ ቡድን እንደመሆኑ መጠን ሲቲንም ነጥብ እንዳያስጥለው ተሰግቷል፡፡ ሮጀርስ ሲቲን ሶስት ነጥብ እንዳያገኝ የሚከለክሉ ከሆነ ደግሞ ለቀድሞ ክለባቸው ሊቨርፑል ውለታ እንደዋሉ ይቆጠራል፡፡

ማንችስተር ሲቲ ሊጉን በ92 ነጥብ ይመራል፤ ሊቨርፑል በ91 ይከተላል፤ ቶተንሃም በ70 ሶስተኛ ደረጃን ሲይዝ ቼልሲ በ68 አራተኛ ደረጃ ተቀምጧል፡፡ አርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ በ66 እና በ65 ነጥብ አምስተኛ እና ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *