loading
ያልተሳካው የህወሃት ቡድን ከሀገር የመውጣት ሙከራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013  የህወሃት አባላት ከሃገር ለመውጣት ያደረጉት ጥረት በመከላከያ ሰራዊት ከሽፏል ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ተናገሩ ሌተናል ጄኔራሉ ደበሌ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ፥ ከሃገር ለመውጣት ከሞከሩት የቡድኑ አባላት መካከል አብዛኛዎቹ መደምሰሳቸውን እና የተወሰኑት ወደኋላ ተመልሰው ሸለቆ ውስጥ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ከሃገር ለመውጣትም መታወቂያ በማዘጋጀትና ስማቸውን በሌላ ማንነት በመቀየር በሱዳንና በአማራ ክልል አቋርጠው ለመውጣት መሞከራቸውንም ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጅ ይህ ሙከራና እቅዳቸው ከሽፎ መደምሰሳቸውን ተናግረዋል፤ ቀሪዎቹም መውጫ ቀዳዳ ስለሌላቸው መከላከያ ሰራዊት እየተከታተለ እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡

በመግለጫቸው በትግራይ ክልል ሄሊኮፕተር ተመቷል ተብሎ በጁንታው አባላት የሚናፈሰው አሉባልታ ሃሰተኛ ወሬ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *