loading
ደቡብ አፍሪካ እስከመጪው ወር አጋማሽ ድረስ 20 የሚሆኑ የድንበር ኬላዎቿን ለመዝጋት ወሰነች::

አዲስ አበባ፣ጥር 04፣ 2013 ደቡብ አፍሪካ እስከመጪው ወር አጋማሽ ድረስ 20 የሚሆኑ የድንበር ኬላዎቿን ለመዝጋት ወሰነች:: ደቡብ አፍሪካ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በፍጥነት እየተስፋፋ የመጣው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ ስላሳሰባት ነው፡፡ ድንበሮቹ ዝግ ሆነው በሚቆይበት ወቅትም ወደ ሀገሪቱ የሚገቡም ሆኑ ወደ ውጭ የሚወጡ ተጓዦች አይኖሩም ነው የተባለው፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ለ20 ሚሊዮን ሰዎች የሚሆን የክትባት መጠን ለማስገባት እየሰራች መሆኑ ተሰምቷል፡፡ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በሰጡት መግለጫ ከተለያዩ ክትባት አምራች ተቋማት ጋር ተስፋ ሰጭ ድርድሮችን ማድረጋቸውንና ክትባቱን ለህዝባቸው ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ክትባቱን ዘገየ ቢባል በዚህ ዓመት አጋማሽላይ ለህዝቡ ማዳረስ እንደሚገባን መግባባት ላይ ደርሰናል ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፡፡
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው በደቡብ አፍሪካ የቫይረሱ ስርጭት በፍጥነት በመጨመሩ ሆስፒታሎችታማሚዎችን ተቀብለው ለማስተናገድ ከአቅማቸው በላይ ሆኖባቸዋል፡፡በደቡብ አፍሪካ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን ይህ ቁጥር ከጠቅላላው አፍሪካ ከ30 በመቶ በላይ በሆኑ ነው የሚነገረው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *