loading
ደቡብ አፍሪካ የጣለችውን የእንቅስቃሴ እቀባ የማቅለል ሂደቷን ወደ ሶስተኛ ደረጃ ከፍ አደረገች::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ደቡብ አፍሪካ የጣለችውን የእንቅስቃሴ እቀባ የማቅለል ሂደቷን ወደ ሶስተኛ ደረጃ ከፍ አደረገች::
ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከመጭው የፈረንጆች ሰኔ 1 ጀምሮ ህዝቡ ወደ መደበኛ እንቅድቃሴው የሚገባበትን መንገድ መቀየሳቸውን አስታውቀዋል፡፡
ፕሪቶሪያ እገዳዎችን ለማንሳት ስትነሳ ባለ አምስት ደረጃ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በማስቀመጥ ነበር፡፡አሁን ሶስተኛውን ዙር ስትጀምር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ሲባል ጥብቅ የሆኑ የጤና መመሪያዎችን በማክበር በርካታ የንግድ ተቋማት ሙሉ ስራቸውን ማካሄድ ይችላሉ ተብሏል፡፡አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ሀገሪቱ ይህን ውሳኔ ያለፈችው በሽታውን በቤት ውስጥ ሆኖ መከላከል ቢቻልም ኢኮኖሚው ክፉኛ ከተጎዳ ሰዎች ለከፋ ችግር እንዳይጋለጡ በመስጋት ነው፡፡ደቡብ አፍሪካ በአሁኑ ጊዜ ከአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ብዙ ሰው ከተያዘባቸው ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ ስትሆን ከ22 ሺህ 500 በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 429 ሰዎች ደግሞ ህይዎታቸው አልፏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *