loading
ደቡብ ኮሪያ የተሰወሩብኝ ባለሰልጣን በጎረቤት ሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተገድለውብኛል ስልት ከሰሰች::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 ደቡብ ኮሪያ የተሰወሩብኝ ባለሰልጣን በጎረቤት ሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተገድለውብኛል ስልት ከሰሰች:: በዓሳ ሀብት ልማት ተቋም ውስጥ ይሰሩ የነበሩት ግለሰብ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ደብዛቸው ጠፍቶ እንደነበር የገለፀችው ሴኡል በመጨረሻ በሰሜን ኮሪያ የባህር ጠረፍ አስከሬናቸው መገኘቱን አረጋግጣለች፡፡

የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ሰውየውን የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተኩሰው ገድለው ሲያበቁ በጭካኔ አስከሬናቸው በእሳት እንዲቃጠል አድርገው እንደጣሉት ደርሸበታለሁ ብሏል፡፡ ይህ ሁኔታም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በድንበር አካባቢ ውዝግብ የበዛበትን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ያሻክረዋል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡

የለሰቡን ግድያ በተመለከተ ከፒዮንያንግ አስቸኳይ ማብራሪያ እንደምትፈልግ ያሳሰበችው ሴኡል በድርጊቱ ላይ የተሳተፉ አካላት ላይ ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲጣልም ጠይቃለች፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ሰሜን ኮሪያ ከጎረቤት ደቡብ ኮሪያ የተሰነዘረባትን ክስ አስመልክታ ምንም አይነት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥባለች፡፡ ሁለቱ ኮሪያዎች ባለፉት ወራት በድንበር አካባቢ ወታደሮቻቸው የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *