loading
ዲዲዬር ድሮግባ ጫማውን መስቀሉን እወቁልኝ ብሏል

ዲዲዬር ድሮግባ ጫማውን መስቀሉን እወቁልኝ ብሏል

አርትስ ስፖርት 13/03/2011

የቀድሞው የአይቮሪ ኮስት እና ቼልሲ ኮከብ ዲዲየር ድሮግባ ከ BBC World Service’s Sportshour ጋር በነበረው ቆይታ በ40 ዓመቱ፤ ከ20 ዓመታት የእግር ኳስ ተጫዋችነት መገለሉን አስታውቋል፡፡

ዲዲየር በቼልሲ ቤት ለሁለት ጊዜ ያህል ስኬታማ ወቅት ያሳላፈ ሲሆን በክለቡ ቆይታው በ381 ጨዋታዎች 164 ጎሎችን በማስቆጠር አራት የፕሪምየር ሊግ፣ አንድ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ እና የኤፍ ኤ ካፕ፣ ሊግ ካፕ እና ሌሎችንም ዋንጫዎች ማሳካት ችሏል፡፡

ያለፉትን 18 ወራት በአሜሪካው የሁለተኛ ዲቪዚዮን ተወዳዳሪ ፎኒክስ ሬይሲንግ በተጫዋነት እና የክለቡ ድርሻ ባለቤትነት ቆይታ አድርጓል፡፡ የመጨረሻ ግጥሚያው ደግሞ በያዝነው የፈረንጆች ህዳር ወር መጀመሪያ ላይ በሊዩስቪሌ ሲቲ የ1 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዶ፤ የድሮግባ የተጫዋችነት ጊዜ መቋጫ ቀን ይጠበቅ ነበር፡፡

የእግር ኳስ ህይወቱን በፈረንሳዩ ሊግ ሁለት ተወዳዳሪ ሌ ማንስ የጀመረ ሲሆን በ2002 ጥር ወር ወደ ሊግ አንድ ተሳታፊው ገንጎ፤ ከዚያም ማርሴ በመቀጠል በ24 ሚሊየን ፓውንድ ዋጋ ወደ ምዕራብ ለንደኑ ቼልሲ በማቅናት ስኬታማ ጊዜውን አሳልፏል፡፡

በጋላታሳራይ፣ ሻንጋይ ሽኑዋና ሞንትሪያል ኢምፓክትም ቆይታም ነበረው፡፡

ድሮግባ በአይቮሪ ኮስት ብሔራዊ ቡድን ቆይታው በ106 ጨዋታዎች 65 ግቦችን በማስቆጠር ባለክብረወሰን ሲሆን ሀገሩን በዓለም እና አፍሪካ ዋንጫዎች አገልግሏል፡፡

በግሉ ከአንድም ሁለቴ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋችነትና የፕሪምየርሊጉን ወርቃማ ጫማ ጨምሮ ሌሎችን ሽልማት ማግኘት ችሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *